Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የ 71 ባለሀብቶች ፍቃድ ተሰረዘ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የ71 ባለሀብቶችን ፍቃድ መሰረዙን የአፋር ክልል የኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ።

በክልሉ ኢንቨስትመንት ላይ የመከረ መድረክ ትናንት በሰመራ ከተማ ተካሂዷል።

በኮሚሽኑ የኢንቨስትመንት ማበረታቻና መረጃ ዳይሬክተር አቶ እድሪስ እስማኤል ÷ባለሀብቶቹ ከአራት አመት በፊት በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ለመሰማራት ፍቃድ ቢወስዱም እስካሁን ወደ ስራ አልገቡም።

ባለሀብቶቹ በክልሉ በቂልበቲ-ረሱ ዞን በአበአላ ከተማ አስተዳደር ለሆቴል ግንባታ የተረከቡት ከ67 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ መሬት ወደ መሬት ባንክ ገቢ መደረጉን አስታውቀዋል።

በክልሉ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ካለው አስተማማኝ ሰላም በተጨማሪ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ፍቃድ አሰጣጥን ጨምሮ ቀልጣፋ አገልግሎት እየተሰጠ በመሆኑ በዘርፉ የሚሰማሩ የአገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል ።

በአመታቱ 116 ባለሃብቶች በእርሻ፣ በእንስሳት ሃብትና በማዕድን ልማት ፍቃድ ወስደው እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ከባለሀብቶቹ ውስጥ 48ቱ ወደ ስራ የገቡና 36ቱ ደግሞ በዝግጅት ምዕራፍ ላይ ያሉ መሆናቸውን የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ ቀሪዎቹ ግንባታ ላይ መሆናቸውን አመልክተዋል።

እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ ባጠቃላይ ባለሀብቶቹ በተሰማሩባቸው መስኮች ከ10 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ጊዜያዊና ቋሚ የስራ እድል መፍጠሩን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.