Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል እና አማራ ክልል አጎራባች ወረዳ የአንበጣ መንጋ ተቀሰቀሰ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል 12 ወረዳዎች ላይ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በእንስሳት መኖ ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ ተገለጸ።
የአፋር ክልል አንበጣ መከላከል ግብረ ኃይል አስተባባሪ የሆኑት አቶ መሀመድ ሠኢድ ፥ ከሀምሌ ወር ጀምሮ ከፌደራል ግብርና ሚኒስቴር ጋር የችግሩን አሳሳቢነት በመመልከት እርምጃ የመዉሰድ ተግባር ተጀምሮ እንደነበር ገልጸዋል።
በመሀል የክትትል ሥራው በመቋረጡ የበረሀ አንበጣዉ በስፋት ሊፈለፈል ችሏል ብለዋል፡፡
አንበጣዉን በምድር ላይ እያለ የማጥፊያ ጊዜዉ በማለፉ፥ የአዉሮፕላል ኬሚካል እርጭት እንደሚያስፈልግ ነው አቶ መሀመድ ሠኢድ የተናገሩት።
በተመሳሳይ የአንበጣ መንጋዉ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን እንዳይገባ የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ የመከላከል ስራ ከዉዲሁ እየሰራ መሆኑን የመምሪያው ምክትል ኃላፊ አቶ አሊ ሰይድ ገልጸዋል።
የአንበጣ መንጋዉ በባለፈው ዓመት መነሻዉን አፋር ክልል በማድረግ በ61 ሺህ የሰብል ምርት አብቃይ አርሶ ደሮች ማሳ ላይ ጉዳት አድርሷል።
በአፋር ክለልል እየተፈለፈለ የሚገኘዉ የአንበጣ መንጋ ስጋት የፈጠረው ከነሐሴ 2013 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን እስካሁን አንበጣዉን አስቀድሞ ለመከላከል የተደረገው ጥረት አነስተኛ እንደሆነ ተገልጿል።
የበርሀ አንበጣ መንጋዉ በአፋር ክልል የተለያዩ ወረዳዎች የስርጭት መጠኑን በማስፋት እየተፈለፈለ ሲሆን፣ ወደ ሌሎች ክልሎች እንዳይዛመት የተቀናጀ ስራ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል ፡፡
በኢሳያስ ገላው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
143
Engagements
Boost Post
129
10 Comments
4 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.