Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጀመረ

አዲ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ያለው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በአፋር ክልል አዋሽ ከተማ አስተዳደር በይፋ ተጀምሯል።
በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስተባባሪነት እየተካሄደ ባለው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ ግብር÷ የወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ዛሬ በአዋሽ የተለያዩ ተግባራትን አከናውነዋል፡፡
ወጣቶቹ በአዋሽ ከተማ አስተዳደር ጎዳና ላይ በመንቀሳቀስ የአካባቢ ፅዳት አከናውነዋል፡፡
በተጨማሪም የእግር ጉዞ በማድረግ ህብረተሰቡ ወጣቱ ይዞት ስለተነሳው ዓላማ የማስገንዘብ እና የማነቃቃት ስራ እንዲሁም የችግኝ ተካላ ማካሄዳቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
የአፋር ክልል የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዑመር መሀመድ ዱባ መርሐ ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ በአሁኑ ወቅትም እንደአገር የተጀመሩ የበጎ ፈቃድ ስራዎችን በክልል ደረጃ በተቀናጀ መልኩ ለማስቀጠል ሰፊ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።
የወጣቶቹ ወደ ክልሉ መምጣት ለከተማው መነቃቃት እንደሚፈጥር ያላቸውን እምነት ገልፀው ለዕቅዱ ስኬትም ሁሉም የክልሉ ማህበረሰብ እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.