Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል 36 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ ተለቀቁ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል የይቅርታ መስፈርትን አሟልተው የተገኙ 36 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ ከእስር እንዲለቀቁ መደረጉን የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ።
የክልሉ ዋና ጠቅላይ አቃቤ ህግ ወይዘሮ ፋጡማ መሐመድ እንደገለጹት÷ ጉዳያቸው ለክልሉ የይቅርታ ቦርድ ቀርቦ ከእስር እንዲለቀቁ የተወሰነላቸው በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ተፈርዶባቸው ይቅርታ እንዲደረግላቸው ከጠየቁ 102 የህግ ታራሚዎች መካከል ነው።
የህግ ታራሚ ይቅርታ እንዲደረግለት በሰራው ወንጀል ከመፀፀቱ ባለፈ ቢያንስ አንድ ሶስተኛ የሚሆነውን የእስር ጊዜውን ማጠናቀቅ ይጠበቅበታል ብለዋል ።
በዚህም መስፈርቱን አሟልተው የተገኙ 36 ታራሚዎች ከትናንት ጀምሮ በይቅርታ ተለቀው ወደ ህብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ የክልሉ የይቅርታ ቦርድ ተገቢነቱን መርምሮ መወሰኑን አስታውቀዋል።
የክልሉ ማረሚያ ቤቶች ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ መሐመድ አህመድ በበኩላቸው÷ በክልሉ የሚገኙ ታራሚዎች አምራች ዜጋ እንዲሆኑ የቀለምና ሙያዊ ሥልጠናዎች የተሰጣቸው መሆኑን ገልጸዋል።
በክልሉ ትናንት ለታራሚዎች የተደረገው ይቅርታ በዓመቱ ሁለት ጊዜ ይቅርታ ለመስጠት የተያዘው እቅድ አካል መሆኑን የክልሉን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.