Fana: At a Speed of Life!

የአፋሩ ጀብደኛ “መሀመድ አሊ”

አዲስ አበባ፣ ጥር 18 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መሀመድ አሊ ጠላት መሣሪያ በሚያሽከረክሩት ሃርድ ቶፕ ላንድ ክሩዘር መኪናቸው ላይ እየተኮሰ አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ታጣቂዎችን ደምስሰው የቆሰሉ 12 የአፋር ልዩ ኃይሎችን በሚያስደንቅ ጀብድ ሆስፒታል ያደረሱ የ62 ዓመት ጎልማሳ ሾፌር ናቸው።

የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ ሾፌር የሆኑት መሀመድ አሊ የእለቱን ውሏቸውን ሲተርኩ፥ ከቤት የወጣሁት እንደ ወትሮው ሁሉ መደበኛ ሥራዬን ለመከወን ነበር ይላሉ።

ከቢሮ የተሰጣቸውን ዕለታዊ የሥራ ትእዛዝ ተቀብለውም ከሰመራ ወደ መጋሌ ወረዳ እንደሄዱም ነው የተናገሩት።

በአፋር ክልል ንጹሃን ላይ ጁንታው በከባድ መሣሪያ እየፈፀመ ያለውን ጥቃት ለመመከት እና ለመደምሰስ ለሚዋደቁ የአፋር አናብስት በመኪናቸው ውሃ ጭነው ለማድረስ ወደ ጦር አውድማው እንደሄዱም መሀመድ አሊ ይዘረዝራሉ።

ጀግናው የ62 ዓመት ጎልማሳ ውሃ አድርሰው ጁንታውን ደምስሰው የቆሰሉ 12 የአፋር ልዩ ኃይል አባላትን ይዘው በመመለስ ላይ እንዳሉ ነበር ጥይት የዘነበባቸው።

መሀመድ አሊ፥ ምንም እንኳ ጁንታው መንገድ ዘግቶ ከፊት፣ ከኋላ እና ከተለያዩ አቅጣጫዎች ከባድ መሣሪያ እና ጥይት እየተኮሰባቸው መሄጃ ቢያሳጣቸውም “ለጁንታው እጄን ከምሰጥ ሞቴን እመርጣለሁ! ” ብለው ቁስለኞቹን የአፋር አናብስት እንደጫኑ ወደ ፊት፣ ወደ ሆስፒታል በፍጥነት እንደነዱ ያስረዳሉ።

ጠላትን በጣጥሰው ሲሄዱ እራሳቸው ላይ ተመተው ቢቆስሉም፣ የመኪናቸው ጎማ ተመቶ በቸርኬው ከ20 ኪሎ ሜትር በላይ ቢሄድም እንደገና ጎማ ቀይረው አናብስቱን በጀግንነት ዱብቲ ሆስፒታል ማድረሳቸውን ለአፋር መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.