Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ እስካሁን ከ12 ሚሊየን በላይ የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራዎች ተካሂደዋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ኮቪድ-19 ምርመራ አጠናክሮ ለመቀጠል ጥሪ መደረጉን ተከትሎ እስካሁን ከ12 ሚሊየን በላይ የላብራቶሪ ምርመራዎች ተደርገዋል፡፡

በዚህም እስካሁን ከተካሄደው የላብራቶሪ ምርመራ 10 በመቶ ያክሉ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

እንደ አፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከላት መረጃ እስካሁን በአፍሪካ ከ1 ሚሊየን 300 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ተይዘዋል፡፡

እንዲሁም ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ32 ሺህ በላይ አልፏል፡፡

ማዕከሉ እስካሁን በአህጉሪቱ ከ 1 ሚሊየን በላይ ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ማገገማቸውን ነው ያስታወቀው።

የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከላት ባለፈው ሳምንት ባወጣው ሪፖርት በአህጉሪቱ በቫይረሱ ከሚያዙት መካከል 81 በመቶዎቹ በአሥር ሀገራት የሚገኙ መሆናቸውን አመልክቷል፡፡

በአለም በስምንተኛ ደረጃ የተቀመጠችው ደቡብ አፍሪካ 22 በመቶውን ስትይዝ፣ ሞሮኮ 21 በመቶ፣ ኢትዮጵያ 14 በመቶ፣ ሊቢያ 10 በመቶ፣ አልጀሪያ 4 በመቶ፣ እንዲሁም ኬኒያ፣ ናይጄሪያ፣ ናሚቢያ፣ ቱኒዚያ እና ግብጽ ሁለት በመቶውን ይይዛሉ፡፡

ምንጭ፡- ሲጂቲኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.