Fana: At a Speed of Life!

በኢራቅ በአንድ የኮሮና ቫይረስ ህክምና መስጫ ሆስፒታል ውስጥ በደረሰ የእሳት አደጋ የ82 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢራቅ በአንድ የኮሮና ቫይረስ ህክምና መስጫ ሆስፒታል ውስጥ በደረሰ የእሳት አደጋ የ82 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡
በአደጋው ሕይወታቸው ካለፉ ሰዎች በተጨማሪ 100 ሰዎች የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል ነው የተባለው፡፡
አደጋው በሆስፒታሉ ውስጥ ያለ የኦክስጅን መያዥያ በመፈንዳቱ የተከሰተ መሆኑ ታውቋል፡፡
እንደ ኢራቁ የሃገር ውስጥ ሚኒስቴር መግለጫ በሆስፒታሉ የእሳት አደጋ መከላከያ ስርዓት አለመኖሩ እሳቱ በፍጥነት እንዲስፋፋ ምቹ ሁሌታን ፈጥሯል፡፡
ምንጭ፡-አልጀዚራ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.