Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለው ጫና አፍሪካን ለማንበርከክ የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው – በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለው ጫና ፓን አፍሪካኒዝም ዳግም እንዲያቆጠቁጥ እየተደረገ ያለውን ጥረት በማኮሰስ አፍሪካን ለማንበርከክ የሚደረግ እንቅስቃሴ መሆኑን በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ይናገራሉ።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት እና ኑሯቸውን በአሜሪካ ሜሪላንድ ያደረጉት አየሁብርሃን ትዕዛዙ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ለስልጣናቸው ሳይሳሱ አገሬን ብሎ በግንባር መሰለፍ አንድም ለአገራቸው መታመናቸውን ሁለትም እኔ ብሄድም እኔን ተክቶ አገሩን የሚያገለግል ሀይል አለ የሚል በራስ መተማመናቸውን ያሳያል ነው ያሉት።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔ እንዳለፋት ተመሳሳይ ግብራቸው ከፍ ብሎ በታሪክ በሚታወሱት መሪዎች ልክ ደምቆ የሚታይ መሆኑን ያነሡት ደግሞ በአሜሪካ ዋሽንግተን ነዋሪዎቹ ካሌብ አማረ እና ዶክተር ብርሃኑ ቡልቻ ናቸው።

ኑሯቸውን በውጭ ያደረጉት እነዚህ ኢትዮጵያውያን እንዳሉት አገርን መታደግ ቁጭ ብለን ከሌላው ሰው የምንጠብቀው ጉዳይ ሳይሆን የእያንዳንዳችንን ተሳትፎ የሚጠይቅ ነው።

አሜሪካ እንዲሁም ሌሎች ምዕራባውያንን የሚቃወሙ ሰልፎችንም ከአፍሪካውያን፣ ሌሎች ጥቁር ህዝቦች እና የኢትዮጵያን እውነት የተረዱ ዜጎችን በማስተባበር እያካሄዱ ያሉትን የተቃውሞ ሰልፎች እንዲሁ አንዲት ኢትዮጵያን ብቻ ለመታደግ ሳይሆን ፓን አፍሪካኒዝምን ለመደፍጠጥ በስውር እና በግላጭ እየተደረገ ካለው ሩጫ ጋር የሚደረግ ፍልሚያ ነው ብለዋል።

እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በግምባር ከጠላት ጋር ከመፋለም እስከ ደጀንነት እንዲሁም በዚሁ ችግር ለተፈናቀሉ ዜጎች “አይዞን ኢትዮጵያ” እና በሌሎችም መንገዶች ድጋፎች መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል ኢትዮጵያውያኑ።

ተገደን የገባንበት ጦርነት ያስከተለውን እና ሊያስከትል የሚችለውን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ በጋራ ክንድ መከላከል ከሁሉም ይጠበቃልም ነው ያሉት።

ይህ ደግሞ እንደ አስተያየት የራስን ምቾት በመገደብ አገር በተጣራች ልክ መልስ ለመስጠት ሁሉም ዝግጁ መሆን እንደሚጠበቅበት አመላካች ነው።

“ዛሬ በሀሳብ ልዩነቶች ማዶ ለማዶ ሆነን ሀሳብ የምንወራወርበት ጊዜ አለመሆኑን” ያነሱት ዶክተር ብርሃኑ ቡልቻ እና ካሌብ አማረ፥ “ስለአገር መቀጠል፣ ስለዜጎች ነጻነት አብዝተን መጨነቅ ሌሎቹን ጉዳዮቻችንን በይደር ማቆየት ይኖርብናል” ብለዋል።

አስተያየት ሰጪዎች የአሸናፊነት ምልክቷ ኢትዮጵያ ከቆረጠው ህዝቧ እና መሪዋ ጋር ይህን ክፉ ጊዜ በድል በመወጣት ጠላቶቿ አንገት የሚደፉበት እንደሚሆን ቅንጣት ጥርጥር የለንም ነው ያሉት።

በአፈወርቅ አለሙ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.