Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ስደተኞች ጉዳይ ላይ የሚመክረው የልዑካን ቡድን ወደ ሳዑዲ አረቢያ አቀና

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ ስደተኞች ጉዳይ ላይ የሚመክረው የልዑካን ቡድን ወደ ሳዑዲ አረቢያ አቅንቷል፡፡
ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎች ባለደርሻ አካላት የተወጣጣ ልዑክ ነው በኢትዮጵያ ስደተኞች ጉዳይ ላይ ለመምከር ወደ ሳዑዲ አረቢያ ያቀናው፡፡
ቡድኑ ከሚመለከታቸው የሳዑዲ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በሳዑዲ የኢትዮጵያውያንን የመብት አያያዝ እና ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበት ሁኔታ ላይ ይመክራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
እንዲሁም በሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች መካከል የሚደረገው ውይይት ህጋዊ ሰነድ የሌላቸውን ስደተኞች በፍላጎት ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በሚደረገው ሂደት ላይ የተገኙ ውጤቶችና እንቅፋቶች ላይ በስፋት ይመክራል ተብሏል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.