Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ሶስት ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 11፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ሶስት ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ እንደተያዙ መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

አንድ የ44 ዓመት ጃፓናዊ ዜጋ፣ 1 የ85 ዓመት ኢትዮጵያዊ እና 1 የ39 ዓመት አውስትራሊያዊ ዜጋ በተደረገላቸው የህክምና ክትትል እና የላቦራቶሪ ምርመራ ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

ይህን ተከትሎም በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 9 አድጓል።

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ከነበሩት ውስጥ አራቱ የህመም ምልክቶችን ማሳየት ያቆሙና በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ሚኒስቴሩ ከትናንት በስቲያ ማሳወቁ ይታወሳል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.