Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ700 ተሻገረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የ17 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፤ በአጠቃላይ በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 709 ደርሷል።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 18 ሺህ 778  የላብራቶሪ ምርመራም 1 ሺህ 545 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 43 ሺህ 688 መድረሱንም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ባወጡት መረጃ አመላክተዋል።

ከዚህ ባለፈ የ17 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 709 መድረሱንም አመላክተዋል።

በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 534 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 15 ሺህ 796 መድረሱም ተገልጿል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን 794 ሺህ 686 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 43 ሺህ 688 ደርሷል።

አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 27 ሺህ 181 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 290 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

እስካሁን በኢትዮጵያ 15 ሺህ 796 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገገሙ፤ የ709 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 2 ሰዎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.