Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ተጨማሪ አንድ ሰው ተገኘ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ተጨማሪ አንድ ሰው መገኘቱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።
 
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ የሚገኝበት ሰው ከተገኘ ወዲህ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ አንድ ተጨማሪ ሰው መገኘቱን ተከትሎ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 12 ደርሷል።
 
ታማሚው የ34 ዓመት ኢትዮጵያዊ ሲሆን፥መጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ከዱባይ ወደ ሀገር ውስጥ የገባ መሆኑን ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።
 
ግለሰቡ የህመም ምልክት የነበረው በመሆኑ መጋቢት 13 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ ጤና ተቋም መሄዱ ተመላክቷል።
 
ለህክምና የሄደበት ተቋም ለኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሪፖረት በማድረጉ ግለሰቡ በተደረገለት የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል ነው ያሉት ሚኒስትሯ።
 
በአሁኑ ወቅት ታማሚው በለይቶ ማቆያ ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገለት ሲሆን፥ ጤንነቱ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።
 
ከታማሚው ጋር የቅርብ ግንኙነት የነበራቸው 15 ሰዎችን ለማግኘት እየተሰራ መሆኑንም ዶክተር ሊያ ጠቁመዋል።
 

መላኩ ገድፍ

 
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.