Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 23 መድረሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስታወቁ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 21 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 23 መድረሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋዊ የፌስ ቡክ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ገልጸዋል።

እስከ ዛሬ ጠዋት ድረስ ከ800 የሚበልጡ ተጠርጣሪዎች የላቦራቶሪ ምርመራ እንደተደረገላቸውም ነው ያስታወቁት።

እስካሁንም ሁለት ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋልም ነው ያሉት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ህብረተሰቡ ከጤና ባለሙያዎች የሚተላለፉ መልዕክትና መመሪያዎችን በአግባቡ በመተግበር ራሱን ከቫይረሱ እንዲጠብቅም ጥሪ አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.