Fana: At a Speed of Life!

በየዓመቱ በኤች አይ ቪ ከሚያዙ ሰዎች ውስጥ 67 በመቶዎቹ ወጣቶች ናቸው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በየዓመቱ በኤች አይ ቪ ከሚያዙ ሰዎች ውስጥ 67 በመቶ የሚሆኑት ወጣቶች መሆናቸውን የፌደራል የኤች ኤይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት ገለጸ።
በኢትዮጵያ በየዓመቱ በኤች አይ ቪ ኤድስ 11 ሺህ 700 መቶ 11 ሰዎች በኤች ኤይ ቪ ኤድስ እንደሚያዙ ነው ጽህፈት ቤቱ ያስታወቀው፡፡
ከዚህም ውስጥ 63 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ሲሆኑ፥ 24 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ከ14 ዓመት በታች ያሉ ህጻናት መሆናቸውን ተነግሯል።
የጽህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጽጌሬዳ ክፍሌ፥በኢትዮጵያ ከ622 ሺህ በላይ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ያለባቸው ሲሆን፥ ከ122 ሺህ በላይ የሚገመቱ የሕብረተሰብ ክፍሎች ቫይረሱ በደማቸው እንዳለባቸው ተመርምረው ያላወቁ እንደሆኑም ተናግረዋል።
አጠቃላይ ቫይረሱ ከሚገኝባቸው ወገኖች ውስጥ 62 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ሲሆኑ፥ በየዓመቱ ደግሞ12 ሺህ የሚገመቱ ዜጎች በኤች ኤይ ቪና ተያያዥ በሽታዎች ህይወታቸውን ያጣሉም ነው ያሉት።
ሕይወታቸውን በኤች ኤይ ቪና ተያያዥ በሽታዎች ከሚያጡት ውስጥም 57 በመቶ ሴቶች ሲሆኑ፥ 16 በመቶ እድሜያቸው ከ14 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ናቸው ብለዋል።
በሲሳይ ሀይሌ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+3
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.