Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ በ2025 የታዳሽ ሀይልን ተደራሽ ለማድረግ 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ያስፈልጋል

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2025 የታዳሽ ሀይልን ተደራሽ ለማድረግ 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጅ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ከዓለም ባንክ፣ ከአውሮፓ ህብረትና ከሌሎች የልማት አጋር አካላት ጋር የገንዘብ ድጋፍን በተመለከተ ውይይት እያካሄደ ነው።

በፈረንጆቹ 2025 በመላ ሀገሪቱ የታዳሽ ሀይልን ሙሉ በሙሉ ለማዳረስ እየሰራ መሆኑንም ሚኒስቴሩ በዚህ ወቅት አስታውቋል።

በኢትዮጵያ የታዳሽ ሀይል በ1998 ዓ.ም በክልል ከተሞች የተጀመረ ሲሆን፥ አሁን ላይ በዚህ አገልግሎት ከ7 ሺህ በላይ የገጠር ከተሞችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ ነው የተገለፀው።

በመላ ሀገሪቱ የታዳሽ ሀይልን በ2025 ተደራሽ ለማድረግ 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግም የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጅ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ፍሬህይወት ወልደሀና ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የተሻለ የኤሌክትሪክ ሀይል እንድታመርትና ተጠቃሚ እንድትሆን አስተማማኝ የሀይል አቅርቦት እንዲኖር ለማስቻል ከመንግስት ባሻገር የግሉ ዘርፍ ሚናም ግንባር ቀደም ሊሆን ይገባዋልም ብለዋል።

በውይይቱ ላይ የክልል እና ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የልማት አጋሮች እየተሳተፉ ነው።

የታዳሽ ሀይል በገጠር ከተሞች የሀይል አቅርቦቱ ተደራሽ እንዲሆን እንዲሁም የገጠር ከተሞች የኢኮኖሚ እድገት እንዲጨምር አስተዋጾኦው ከፍተኛ ነው ተብሏል።

በሲሳይ ጌትነት

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.