Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት ብቻ 704 ሰዎች ላይ የኮሮናቫይረስ መገኘቱን ተከትሎ ከፍተኛ እለታዊ ቁጥር ሆኗል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 7 ሺህ 334 የላብራቶሪ ምርመራ 704 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን ይህም  ከፍተኛው ቁጥር መሆኑን  የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 10 ሺህ 207 መድረሱንም ሚኒስቴሩ ባወጣው ሪፖርት አመላክቷል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከልም 551 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 39 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 30 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣26 ከጋምቤላ ክልል ፣  3 ሰው አፋር ክልል፣ 3 ሰዎች ከሐረሪ ክልል፣ 10 ሰዎች ከድሬ ደዋ አስተዳደር፣ 3 ሰዎች ከሶማሌ ክልል፣ 21 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 11 ሰዎች ከሲዳማ ክልል፣5 ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል  እንዲሁም 2 ሰዎች ከደቡብ ክልል ናቸው።

ከዚህ ባለፈ የ3 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በቫይረሱ ሕይወታቸው ያለፉ ቁጥር 170 መድረሱንም ነው ሚኒስቴሩ በእለታዊ ሪፖርት ያመላከተው።

በዛሬው ዕለት 196 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 5137 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን 331 ሺህ 266 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 10 ሺህ 207 ደርሷል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.