Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት 119 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3ሺህ 895 የላብራቶሪ ምርመራ 119 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ይህንን ተከትሎም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5 ሺህ 689 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ ባወጡት ሪፖርት አመላክተዋል።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 87 ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን  4 ናሙናዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 98 መድረሱን ገልፀዋል።

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት 117 ሰዎች (78 ከአዲስ አበባ፣ 35 ከትግራይ ክልል እና 4 ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር  ) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 132 ደርሷልም ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.