Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ቀናት ናሙና ከሰጡ ግለሰቦች መካከል 13 በመቶዎቹ ኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ከየካቲት 11 እስከ የካቲት 17 ድረስ ናሙና ከሰጡ ግለሰቦች መካከል 13 በመቶዎቹ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ይህንን ያለው የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ነው፡፡

ባለፉት ሰባት ቀናት ብቻ 79 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

በዚህም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ አስከፊነቱ እየጨመረ እንደሚገኝ ነው ኢንስቲትዩቱ ያስታወቀው፡፡

ባለፉት 7 ቀናት 47 ሺህ 204 ናሙና ከሰጡት ግለሰቦች ውስጥ 5 ሺህ 927ቱ በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

ወደ ፅኑ ህሙማን ህክምና ክፍል የሚገቡ ግለሰቦች ቁጥርም በየዕለቱ እያሻቀበ እንደሚገኝ ጠቅሷል።

እስከ ትናንትናው ዕለት ብቻ 386 ሰዎች በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፡፡

በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ከሚገኙት መካከል 61 ህሙማን በመተንፈሻ ማሽን ዕገዛ ላይ እንደሚገኙ ነው ኢንስቲትዩቱ የገለጸው፡፡

በቫይረሱም ህይወታቸውን የሚያጡ ግለሰቦች ቁጥርም እየጨመረ መምጣቱን ገልጾ እስካሁን 2 ሺህ 316 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ሕብረተሰቡ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ይህንን እውነታ በመገንዘብ የጥንቃቄ መንገዶችን በሚገባ መተግበር እንዳለባቸው አስገንዝቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.