Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት 1 ሺህ 778 ሰዎች ቫይረሱ ሲገኝባቸው 20 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 14፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 21 ሺህ 456 የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 778 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 35 ሺህ 836 መድረሱንም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ባወጡት መረጃ አመላክተዋል።

ከዚህ ባለፈ የ20 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 620 መድረሱንም አመላክተዋል።

በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 228 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 13 ሺህ 536 መድረሱም ተገልጿል።

በኢትዮጵያ እስካሁን 694 ሺህ 093 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደርጎላቸዋል።

አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው እና የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው የሚገኝ ሰዎች ቁጥር 21 ሺህ 678 ሲሆን፥ ከእነዚህም 248 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.