Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት 689 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ 7 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 8 ሺህ 023 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 689 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 68 ሺህ 820 ደርሷል።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የ 7ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በዚህም በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎቸ ቁጥር 1 ሺህ 96 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ያሰፈሩት መረጃ ያመለክታል።

በ24 ሰዓታት ውስጥ 375 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 28 ሺህ 314 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

39 ሺህ 408 ሰዎች በአሁን ወቅት ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሲሆን 290 ፅኑ ህሙማን ደግሞ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል ተብሏል።

በኢትዮጵያ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 202 ሺህ 818 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.