Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት 889 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ 12 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 8 ሺህ 115 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 889 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 69 ሺህ 709 ደርሷል።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የ 12ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

በዚህም በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎቸ ቁጥር 1 ሺህ 108 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ያሰፈሩት መረጃ ያመለክታል።

በ24 ሰዓታት ውስጥ 320 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 28 ሺህ 634 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

39 ሺህ 965 ሰዎች በአሁን ወቅት ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሲሆን 301 ፅኑ ህሙማን ደግሞ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል ተብሏል።

በኢትዮጵያ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 210 ሺህ 933 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.