Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 600 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 6 ሺህ 548 የላቦራቶሪ ምርመራ 600 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 88 ሺህ 434 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 471 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ ይህን ተከትሎ በአጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 42 ሺህ 99 መድረሱንም አስታውቋል።

በተጨማሪም ባለፉት 24 ሰአታት የ9 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 346 ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 44 ሺህ 867 ሰዎች መካከል 299 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊየን 390 ሺህ 197 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.