Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር በማካሄድ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት እንደግፋለን – የአውሮፓ ህብረት

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር በማካሄድ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፍ የአውሮፓ ህብረት አስታወቀ።

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ቢሮ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በየዓመቱ ግንቦት 9 የሚከበረውን ”የአውሮፓ ቀን” አስመልክቶ ዛሬ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

ቀኑ 72 ዓመታት ያስቆጠረውን የአውሮፓ ህብረት ምስረታ ታሳቢ በማድረግ የሚከበር መሆኑ ይታወቃል፡፡

በመርሐ ግብሩም ህብረቱ ከኢትዮጵያና አፍሪካ ህብረት ጋር ያለውን ትብብር የሚዳስሱ ሃሳቦች ቀርበዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ተወካይ አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ በዚሁ ወቅት እንደገለጹጽ÷ ህብረቱ ከኢትዮጵያ ጋር ጠንካራ ስትራቴጂካዊ ግንኙነት አለው፡፡

በዚህም ህብረቱ ከኢትዮጵያ ጋር በሰላምና ጸጥታ፣ በንግድ፣በትምህርትና ሌሎች ዘርፎች በትብብር እየሰራ ስለመሆኑም ነው የገለጹት፡፡

የአውሮፓ ህብረትና ኢትዮጵያ ጠንካራ የንግድ ልውውጥ አጋርነት እንዳላቸው ጠቅሰው÷ከኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ መካከል 20 በመቶ የሚሆነው ወደ አውሮፓ ህብረት አባል አገራት እንደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡

ይህም ህብረቱ ከኢትዮጵያ ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ነው ያሉት፡፡

ህብረቱ ከተመሰረተባቸው ዓብይ ዓላማዎች መካከል ሰላምን ማረጋገጥ አንዱ መሆኑን ገልጸው÷ ከዚህ አኳያ ህብረቱ ሰላምን ለማስፈን የሚደረጉ ጥረቶችን ያበረታታል ነው ያሉት፡፡

በኢትዮጵያ ሊካሄድ የታሰበው አገራዊ ምክክር በአገሪቱ ዘላቂ ሰላምን በማስፈን ረገድ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ለአገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት ድጋፍ እንደሚያደርግም ነው የተናገሩት፡፡

በአፍሪካ ህብረት የአውሮፓ ህብረት ጉዳይ አስፈጻሚ ፓትሪክ ዱፖንት በበኩላቸው የአውሮፓ ህብረት፣ በአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ እንዲሰፍንና የተረጋጋ የፖለቲካ ሂደት እንዲኖር ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ህብረቱ በተለይ በአህጉሪቱ በኢኮኖሚ መስክና በተለያዩ ዘርፎች ትስስር እንዲኖር እየደገፈ ስለመሆኑ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.