Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ የእስራኤል ባለሀብቶችን ቀልብ ስቧል – አምባሳደር ራፋኤል ሞራቭ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃ የእስራኤል ባለሀብቶችን ቀልብ መሳቡን በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ራፋኤል ሞራቭ ገለጹ።

በእስራኤል የኢትዮጵያ ኤምባሲና የእስራኤል አፍሪካ የንግድ ምክር ቤት በመተባበር በኢንቨስትመንት ጉዳይ ላይ የተዘጋጀ የበይነ መረብ የውይይት መድረክ ትናንት ተካሄዷል።

በውይይቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ጽዮን ተክሉ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁንና በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ራፋኤል ሞራቭ ተሳትፈዋል።

በእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካና ላቲን አሜሪካ ኢኮኖሚ ጉዳዮች ዳይሬክተር ሚሃል ጉር-አርዬህ፣ የእስራኤል ባለሃብቶች የንግድ ማህበረሰብ አባላት እንዲሁም በግብርና፣ በማምረቻ እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎች ተወካዮች መሳተፋቸው ነው የተገለጸው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ጽዮን ተክሉ መንግስት ነጻነትን እና ብልጽግናን በኢትዮጵያ ለማስፈን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎችን እየወሰደ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

“ከማሻሻያ እርምጃዎች ውስጥ በግሉ ዘርፍ የሚመራ ሁሉን አቀፍና ዘላቂ ልማት መፍጠር አንዱ ነው” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.