Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የመስኖ ልማት እንዲስፋፋ እስራኤል የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ ትቀጥላለች- ራፋኤል ሞራቭ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ የመስኖ ልማት እንዲስፋፋ እስራኤል የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ራፋኤል ሞራቭ ተናገሩ።

በኢትዮዽያ የእስራኤል አምባሳደር ራፋኤል ሞራቭ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ አድርገዋል።

ኢትዮጵያ እና እስራኤል ለረጀም ዓመታት የዘለቀ ግንኙነት አላቸው።

ሁለቱ ሀገራት ካላቸው ግንኙነት አንፃር ግን በምጣኔ ሀብታዊ የግንኙነት መስመር ወይም ኢኮኖሚክ ዲፕሎማሲ ብዙ ርቀት የተጓዙ አይደሉም።

አምባሳደር ራፋኤል ሞራቭ አሁን ላይ በግብርናው ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት የሚያሳዩ የእስራኤል ኩባንያዎችም እየተበራከቱ መምጣታቸውን ተናግረዋል።

በግብርናው በተለይም በጥልቅ የመስኖ ልማት ዘርፍ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው የእስራኤል ኩባንያዎች አይናቸውን ኢትዮዽያ ላይ እየጣሉ ነው ብለዋል።

አምባሳደር ራፋኤል ሞራቭ በመጪው አዲስ ዓመት የኮሮና ቫይርስ ተፅእኖ እያሳደረበት ያለውን የቱሪዝም ዘርፍ ዳግም እንዲያንሰራራ ለማድረግ በሁለቱ ሀገራት መካከል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ እንዲጠናከር ይደረጋል ብለዋል።

እንዲሁም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል እስራኤል ለኢትዮዽያ የህክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ እያደረገች ነው ብለዋል።

በስላባት ማናዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.