Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የሚገኙ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኀን ወኪሎች የእንጦጦ ፓርክን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መቀመጫቸውን በኢትዮጵያ ያደረጉዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኀን ወኪሎች የእንጦጦ ፓርክን ጎበኙ።

ጉብኝቱን የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳዘጋጁት ነው የተገለጸው።

የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ መገናኛ ብዙኀኑ ኢትዮጵያን ለተቀረው ዓለም ለማስተዋወቅ ጠቃሚ ሥራ እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የጉብኝቱ ዓላማ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኀኑ በሃገሪቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተመዘገበውን ዘርፈ ብዙ ለውጥ እንዲያውቁ ለማድረግ እንደሆነም ገልፀዋል።

በተጨማሪም መርሃግብሩ ከጉብኝት ባለፈ ጋዜጠኞችን መረጃ ከሚያገኙበት ተቋማት ጋር በማስተዋወቅ በቀጣይ ዘገባቸው የተሟላ እንዲሆን ለማድረግ ያለመ ነውም ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለውን ለውጥ በአግባቡ እንዲረዱ ለማድረግ መሆኑንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል፡፡

በጉብኝቱ የተሳተፉ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኀን ወኪሎች በበኩለቸው በጉብኝቱ መደሰታቸውን ገልጸው፣ ፓርኩ የሃገሪቱን የቱሪዝም መዳረሻ ቁጥርና ገቢ ከፍ እንደሚያደርግም አንስተዋል።

ፓርኩ በአዲስ አበባ መገኘቱ ጎብኚዎች ወደ ሌሎች የሃገሪቱ አካባቢዎች ጉዞ ለማድረግ ሲያስቡ እንደ መሸጋገሪያ ለመጠቀም እንደሚያገለግል መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.