Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ለ125ኛው የአድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤፍጌኒ ተረክህን ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ለ125ኛው የአድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

አምባሳደሩ “የአድዋ ድል ኢትዮጵያ ቅኝ ግዛትን በመታገልና በማሸነፍ ነጻነቷንና ሉዓላዊነቷን ያስከበረችበት ነው” ብለዋል፡፡

“ድሉ የኢትዮጵያን ህዝብና በወቅቱ የነበሩ አመራሮችን ሃያልነት ያረጋገጠ ብቻ ሳይሆን፥ ሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ነፃነታቸውን እንዲጎናጸፉ በር የከፈተ ነበርም ነው” ያሉት፡፡

ከዚህ ባለፈም መላው አፍሪካውያንን ያነቃቃ እና ብሎም ኢትዮጵያን የአፍሪካውያን የነፃነት ቀንዲል ለመሆን ያስቻላት መሆኑንም” ገልጸዋል፡፡

አምባሳደሩ በመልዕክታቸው “የአድዋ ድል የህዝቦች አንድነት ለጋራ ድል እንደሚያበቃና ለአሁኑም ሆነ ለመጭው ትውልድ ትምህርት የሚሆን ድል ነው” ብለዋል አምባሳደሩ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.