Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር አሜሪካ በአስቸጋሪ ሰዓት በነበረችበት ወቅት ድጋፍ ላሳዩ ኢትዮጵያውያን ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 30 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በካፒቶል ሒል ጥቃት በተፈፀመበት አስቸጋሪ ሰዓት ድጋፋችሁን ለገለፃችሁ አትዮጵያውያን ልባዊ ምስጋና ይድረሳችሁ ሲሉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ራይነር ገለፁ።

የአሜሪካ ኮንግረስ የተመራጭ መራጮች ድምፅ ቆጠራ በማጠናቀቅ  ጆ ባይደን እና ካማላ ሃሪስ ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸውን ማረጋገጡን አምባሳደሩ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ከሁለት ሳምንት በኋላም ቃለ መሃላ እንደሚፈፅሙ እና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንደሚኖር  ነው አምባሳደሩ የገለፁት።

በካፒቶል ሒል ሁከትን የቀሰቀሱ እና በአሜሪካ ዴሞክራሲ ላይ ያመፁ ወንጀለኞች በአሜሪካ ህገ መንግስት መሰረት ተጠያቂ ይሆናሉም  ብለዋል።

በመልዕክታቸውም በአስቸጋሪ ሰዓት ላይ ድጋፋቸውን ለገለፁ ኢትዮጵያውያን ልባዊ ምስጋና ይድረሳቸውም ነው ያሉት አምባሳደሩ።

በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለው ዘላቂ ወዳጅነት እና ትብብር አሁንም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.