Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ያለበት ደረጃ ለማወቅ በሃገር አቀፍ ደረጃ ጥናት ሊካሄድ ነው 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን በተመለከተ በሃገር አቀፍ ድረጃ ጥናት ሊጀመር መሆኑን የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

በጥናቱ ላይ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጨምሮ የጤና ሚኒስቴር፣ የዓለም ጤና ድርጅትና የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከልና የኦሃዮ ዩኒቨርሲቲ ተሳታፊ ናቸው ተብሏል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ ተቋማቱ በዛሬው ዕለት በጋራ ጋዜጣዊ መገለጫ ጥተዋል፡፡

በጋራ በሚያጠኑት ጥናት በሃገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ክልሎች በከተማ እና በገጠር የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ሁኔታ ለማወቅ እንደሚረዳ በመግለጫው ወቅት ተነስቷል፡፡

የጥናቱ ዋና አላማ በሀገር አቀፍ ደረጃ፣ በክልሎችና በከተማ መስተዳድሮች የበሽታው ስርጭት በሁሉም የእድሜ ክልል የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ምን እንደሚመስል ጥናት በማካሄድ በሽታውን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ ላይ መፍትሄ ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

የኮሮና ቫይረስ ህክምና አማካሪ ቦርድ ተወካይ የሆኑት ዶክተር አበባው ገበየሁ የጤና ሚኒስቴር የኮቪድ-19 በሽታን በተመለከተ በርካታ ስራዎች መስራቱን ጠቅሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና አርማ ወርሃንሰን ምርምር ኢንስቲትዩት እንዲሁም የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በርካታ ጥናቶችን እንዲያደርጉ ከጤና ሚኒስቴር ድጋፍ መደረጉንና በጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር የሚመራ የከፍተኛ ባለሙያዎች ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ስራ እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚደረገውን የኮቪድ-19 ጥናት ካለው በርካታ ልምዶች አንጻር እና የተለያዩ ተቋማትን እና አጋር ድርጅቶችን በማስተባበር ጥናቱን እንዲመራ ኃላፊነት እንደተሰጠው ጠቅሰዋል፡፡

ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በሽታውን ለመከላከል በሚደረግው ጥረት አስፈላጊውን መረጃዎች በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ መጠየቁን ከሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.