Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት አስታወቀ፡፡

ኢንስቲቲዩቱ ‘‘በየዕለቱ የማስጠንቀቂያ መልዕክቶችን እያስተላለፍን ብንገኝም በህብረተሰቡ ዘንድ ባለው መዘናጋት እና የወረርሽኙ ስርጭት መጨመር ምክንያት ወረርሽኙ እየጨመረ ይገኛል’’ ብሏል፡፡

በዚህም በቫይረሱ የሚያዙ፣ ህይወታቸውን የሚያጡ እና ወደ ፅኑ ህሙማን ህክምና ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ መጨመሩን ከኢንስቲቲዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

እንደአብነትም በትናንትናው ዕለት ለ7 ሺህ 686 የላቦራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን÷ 985 ግለሰቦች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

ይህ ማለት ናሙና ከሰጡ 100 ግለሰቦች 13ቱ (13 በመቶዎቹ) የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

በአንድ ቀን 19 ግለሰቦች ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የገቡ ሲሆን÷ በአጠቃላይ 448 ግለሰቦች በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ይገኛሉም ብሏል።

10 ግለሰቦች ደግሞ በትናንትናው ዕለት ህይወታቸውን ማጣታቸውን ኢንስቲቲዩቱ አስታውሷል።

ስለሆነም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የሐይማኖት ተቋማት ፣ ሲቪክ ማህበራት፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፣ የጤና ባለሙያዎች ፣ መምህራንና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የከፋ ችግር እንዳያስከትል በጋራ የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶችን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.