Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ክትባት በተቀናጀና በታቀደው መሰረት እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ክትባት በተቀናጀና በታቀደው መሰረት እየተሰጠ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ክትባቱ በታቀደው መሰረት በመላው ሀገሪቱ በተሳካ ሁኔታ  መሰጠቱን ቀጥሏል ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡

እስካሁን  በርካታ የጤና ባለሙያዎች መከተባቸውን ያስታወቀው ሚኒስቴሩ ይህ ሪፖርት እስከ ተጠናቀረበት ድረስ የክትባት አስጣጡ ፕሮግራም  በአግባቡ እየተካሄደ እና እስካሁን  ጥቂት  ሰዎች  ላይ  ቀላልና  የሚጠበቁ  አንደ  ማላብ ፣ ማቅለሽለሽ  የመሳሰሉ  የጎንዮሽ  ስሜቶች  በስተቀር  ይህ  ነዉ  የሚባል  አሳሳቢ  የጎንዮሽ  ጉዳት አልተከሰተም ነው ያለው፡፡

በኢትዮጵያ እየተሰጠ ያለው የኮቪድ-19 ክትባት የፈቃዱን የአፈፃፀም መመሪያ መስፈርት ያሟላ ሲሆን የክትባቱ ደህንነትን ለመከታተል ም የሚያስችል የቁጥጥር ስርዓት ተዘርግቷል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ኮቫክስ ከተሰኘ አለም አቀፍ ጥምረት 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ክትባት ዕሁድ የካቲት 28 ቀን 2013 ዓ.ም  የመጀመሪያውን ዙር  መረከቡ እና  የጤና ሚኒስቴርም  ክትባቱ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የህብረተሰብ  ክፍሎች ባለፈው ቅዳሜ መስጠት መጀመሩ የሚታወስ ነው።

ክትባቱ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ብሎም በወረርሽኙ ሊከሰት የሚችለውን ሞት እና ጽኑ ህመምን ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀነስ የሚያግዝ ነው::

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.