Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የዴልታ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ ነው -ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ የዴልታ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዲኤታው ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ተናገሩ።
ዶክተር ደረጀ ዱጉማ በተለይ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ የቫይረሱ ስርጭት መስፋፋት በቫይረሱ የሚያዙ፣ በፅኑ የሚታመሙና ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎችን ቁጥርም እንዲያሻቅብ ማድረጉን ተናግረዋል።
ሚኒስትር ዲኤታው ከትናንት ምሽቱ የዜና መፅሄት ጋር ባደረጉት የስልክ ቃለ ምልልስ ፣ ለዴልታ የኮሮና በቫይረስ ስርጭት መስፋፋት፣ የመከላከልና የጥንቃቄው ስራ መቀዛቀዝ አንዱ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል።
ህዝባዊ መሰባሰቦች መብዛታቸውና የህብረተሰቡ በሚፈለገው መጠን ክትባት አለመከተብም ተጨማሪ ምክንያቶች ናቸው ነው ያሉት።
በትናንትናው እለት ብቻ 38 ሰዎችን በቫይረሱ ህይወታቸውን ሲያጡ ከ750 በላይ ሰዎች ደግሞ በፅኑ  መታመማቸውም ነው የተገለጸው።
ከዚያም ባለፈ በ7 ቀናት ውስጥ 182 ሰዎች በማእከላት ውስጥ መሞታቸው ነው የተነገረው።
የጥንቃቄው መዘናጋት በዚሁ ከቀጠለ ጉዳቱ የከፋ ሊሆን እንደሚችልም ነው ሚኒስትር ዲኤታው የተናገሩት።
የሚፈራው ጉዳት እንዳያጋጥምም ህብረተስቡ ራሱን ከቫይረሱ ለመጠበቅ መወሰንና መተግበር ይገባዋል ፣ ክትባቱንም ሊወስድ ያስፈልጋል ነው ያሉት።
የህግ አካላትም ለመመሪያው ተፈፃሚነት ክትትልና ቁጥጥር ሊያደርጉና ተቋማትም ለመመሪያው መተግበር የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
በትእግስት ስለሺ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.