Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ 6 ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሰ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 5ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ እና ነገ ቀጥለው ይካሄዳሉ።

በዛሬው እለት ስድስት ጨዋታዎች የሚካሄዱ ሲሆን፥ ሁሉም ጨዋታዎች በክልል ከተሞች የሚደረጉ ይሆናል።

በዚህም ወላይታ ዲቻ ከወልቂጤ ከተማ፣ ስሹል ሽረ ከአዳማ ከተማ እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ይገናኛሉ።

ከዚህ ባለፈም ሃዲያ ሆሳዕና ባህርዳር ከተማን ሲያስተናግድ፣ ሃዋሳ ከሲዳማ ቡና እንዲሁም ጅማ አባ ጅፋር ከቅዱስ ጊዮርጊስ ይጫወታሉ።

በነገው እለት ደግሞ ሰበታ ከተማ ፋሲል ከነማን ሲያስተናግድ ከነገ በስቲያ ሰኞ ደግሞ መቐለ 70 እንደርታ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሚጫወቱ ይሆናል።

ሁሉም የዛሬ ጨዋታዎች 9 ሰዓት ላይ የሚደረጉ ይሆናል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.