Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 11ኛ ሳምንት በሃዋሳ ከተማ ስታዲየም ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 5 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የመጀመሪያዋን ጎል በ21ኛው ደቂቃ ላይ ሀብታሙ ገዛኸኝ ሲያስቆጥር፥ በ59 እና በ70ኛው ደቂቃ አዲስ ግደይ ኳሷን ከመረብ አገናኝቷል።

በ66ኛው ደቂቃ ደግሞ ይገዙ ቦጋለ አራተኛውን ጎል ያስቆጠረ ሲሆን፥ በ69 ደቂቃ አበባየሁ ዮሐንስ የመጨረሻውን ጎል ማስቆጠር ችሏል።

እስከ ጨዋታው ፍፃሜ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ግብ ሳያስቆጠር ቀርቷል።

በዚህም ሲዳማ ቡና በ12 ነጥብ እና በ6 ጎል ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.