Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ 157 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ለ3 ሺህ 693 የላቦራቶሪ ምርመራ 157 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም በአጠቃላይ በሀገሪቱ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5 ሺህ 846 ደርሷል።

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 97 ወንዶችና 60 ሴቶች ሲሆኑ የእድሜ ክልላቸውም ከ7 እስከ 83 ዓመት ውስጥ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገልፀዋል።

ከጠቅላላው የላቦራቶሪ ምርምራ ውስጥ 52 ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላቦራቶሪ ምርምራ ሲሆን 4 ሰዎች (3 ሰዎች ከአዲስ አበባ እንዲሁም 1 ሰው ከትግራይ) የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በህክምና ማዕክል ህክምና ላይ የነበረ የ18 ዓመት ወጣት የአዲስ አበባ ነዋሪ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወቷ ያለፈ ሲሆን በጠቅላላ አምስት ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ህይወታቸው አልፏል፡፡

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 103 ደርሷል።

በሌላ መልኩ በትናንትናው ዕለት 298 ሰዎች 200 ከአዲስ አበባ፣ 87 ከሶማሌ ክልል፣ 9 ከአማራ ክልል፣ 1 ከድሬዳዋ ከተማ እና አንድ ከኦሮሚያ ክልል ያገገሙ ሲሆን በዚህም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 430 መድረሱ ነው የተነገረው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.