Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ 2 ነጥብ 1 ሚሊየን ሄክታር መሬት በወራሪ መጤ እፅዋት ዝርያዎች መያዙ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ 2 ነጥብ 1 ሚሊየን ሄክታር መሬት በወራሪ መጤ እፅዋት ዝርያዎች መያዙን የአካባቢ፣ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ገለፀ፡፡

በተጨማሪም እስካሁን 35 ያህል የሚሆኑ የወራሪ መጤ ዝርያዎች መለየታቸውን ገልጿል።

በመሆኑም በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ አይነታቸው እየተስፋፉ የመጡና የተለያየ ዝርያ ያላቸውን ወራሪ መጤ እጽዋት ለማጥፋት የሚሰሩ ስራዎች የሚመራበት ብሄራዊ ስትራተጂና የድርጊት መርሀ ግብር ተጠናቆ ለትግበራ ይፋ ተደርጓል።

በብሄራዊ ደረጃ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት አባል የሆኑበት ኮሚቴ ተቋቁሞ ጥናት ሲካሄድ መቆየቱም ነው የተገለጸው።

የትግበራ ስልቱ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት ተካሂዶበትና ግብዓቶች ተሰጥተውበት ለትግበራ ዝግጁ መሆኑ ተገልጿል።

እንቦጭን ጨምሮ በአገሪቱ እየተስፋፉ የመጡት እነዚህ መጤ ወራሪ የአረም እጽዋቶች ለመከላከል የሚያስችል ተቋማዊ አደረጃጀት እንደሚያስፈልግ በጥናት መጠቆሙን የገለጸው የኮሚሽኑ ÷ ለተለዩት ግቦችና ተግባራት መሣካት የሚያስፈልግ የሀብት መጠን በጥናቱ ተለይቷል ብሏል።

ብሄራዊ ስትራተጂና የድርጊት መርሀ ግብር ተጠናቆ ለትግበራ ይፋ በተደረገበት ወቅት የአካባቢ፣ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ ÷የስትራተጂው ወደ ተግባር መግባት ባልተቀናጀ ሁኔታ ሲደረጉ የቆዩ ጥረቶችን ለማቀናጀትና ለማጣጣም ያግዛል ብለዋል።

የስትራተጂውን መተግበር የአካባቢያዊና የብዝሀ ሀብታችንን ለመጠበቅ ይረዳል ማለታቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.