Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮ-ጅቡቲ መስመር የሚገኘው የዳጉሩ ድኪል መንገድ ጥገና ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኢትዮ-ጅቡቲ የድኪል-ጋላፊ መንገድ ውስጥ ከዳጉሩ እስከ ድኪል 80 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን መንገድ ለማስተካከል የሚያስችለው የጥገና በይፋ ተጀምሯል።

በጥገና ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዲኤታዎች አቶ ካሳሁን ጎፌ እና አቶ አወል ወግሪስ፣ የጂቡቲ የትራንስፖርት እና መሠረተ-ልማት ሚኒስትር ሙሳ ሙሐመድ፣ በጂቡቲ የኢፌዴሪ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዮናስ አያሌው እና በጂቡቲ የወደቦች እና ነፃ ቀጠና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቡበከር ዑመር ሐዲ እና ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተገኝተዋል።

የትራንስፖርት ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ የመንገዱ መስተካከል በኮሪደሩ ለሚያልፈው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ወጪ እና ገቢ የንግድ እንቅስቃሴ እገዛ ያደርጋል ብለዋል።

የድንበር ተሻጋሪ ኢትዮጵያውያን አሽከርካሪዎች ችግር ሆኖ የቆየውን መንገድ ለማስተካከል ሥራው እንዲጀመር ከፍተኛ ጥረት ላደረጉት የኢትዮጵያ እና ጂቡቲ መንግሥታት ምስጋና አቅርበዋል።

በቅርቡ ተጠናቆ ሥራ የጀመረው የዳጎሩ-ጋላፊ የ20 ኪሎ ሜትር መንገድ፣ የታጁራ-በልሆ ኤሊዳር ኮሪደር እና የጂቡቲ-ደወሌ-ድሬዳዋ ኮሪደር ሁለቱ ሀገራት ወደ ምጣኔ-ሀብት የሚያደርጉትን ፈጣን ግስጋሴ በተግባር የሚያሳይ እነደሆነ መግለጻቸውን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.