Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት ደኅንነት ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት ደኅንነት ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት እና ቅንጅታዊ አሰራርን ለማጠናከር የሚያግዝ የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል፡፡

ስምምነቱን የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር፣ የኢትዩ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አገልገሎት፣የኦሮሚያ ክልል ትራንስፖርት ኤጀንሲና የአፋር ክልል ትራንስፖርት ቢሮ ናቸው የተፈራረሙት፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በርኦ ሀሰን በዚሁ ወቅት እንደገለጹት÷ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ደህንነት ላይ የተጋረጠውን አደጋ ለመከላከል የመግባቢያ ስምምነቶች ያስፈልጋሉ፡፡

የኢትዩ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አገልገሎት አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አብዲ ዘነበ በበኩላቸው÷በባቡር መስመሩ የሚታዩ የደህንነት ችግሮች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት የሚፈታ በመሆኑ ይህ የምክክር እና መግባቢያ ሰነድ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከሶማሌ ክልል እና ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ ከዞንና ከወረዳ የፀጥታ መዋቅሮች ጋር ተመሳሳይ የመግባቢያ ስምምነት እንደሚፈረም መገለጹን ከትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.