Fana: At a Speed of Life!

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ኩባንያዎች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች መፍታት የሚያስችል ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ህዳር 21፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚገኙ ኩባንያዎች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች መፍታት የሚያስችል ውይይት ተካሂዷል፡፡

በውይይት መድረኩ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ ፣ ስራ አስኪያጆች እና ከኢንዱስትሪ ፓርኮች የተውጣጡ አምራች ባለሃብቶች ተገኝተዋል፡፡

ውይይቱ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ሲያደርጉ የሚያጋጥማቸውን ችግር ለመለየትና ለችግሮችም መፍትሄ ለማስቀመጥ የሚያስችል መሆኑን ዶክተር እዮብ ተካልኝ ተናግረዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ በበኩላቸው÷የውይይት መድረኩ ባለሃብቶች እያጋጠሟቸው ያሉ ችግሮችን በመለየት ዘለቄታዊ መፍትሄ ለማስቀመጥ አይነተኛ ሚና እንዳለው አስረድተዋል፡፡

ባለሃብቶችን የሚያስተጓጉሉ ችግሮችን በግልጽ ለማስቀመጥ እና በጋራ በመስራት የሁለትዮሽ ጠቀሜታን እውን ለማድረግ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

አሜሪካ አጎዋን ለመዝጋት የሄደችበት የተሳሳተ አካሄድ ማስተካከያ እንዲደረግበት እየተሰራ መሆኑን ነው ዋና ስራ አስፈጻሚው የተናገሩት፡፡
የገበያ አማራጮች እና የሀገር ውስጥ ገበያን በተመለከተ መንግስት ቁርጠኛ ሆኖ በጥናት ላይ የተመሰረቱ መፍትሄዎችን ለማስቀመጥ እየሰራ እንደሆነም አክለዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎችም በሀሰት ፕሮፖጋንዳ አንረበሽም፤ በየትኛውም ሁኔታ ከኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ጎን እንቆማለን ማለታቸውን ከኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.