Fana: At a Speed of Life!

በኢንዶኔዥያ 50 ተጓዦችን ይዞ ሲበር የነበረ ቦይንግ 737 የደረሰበት አልታወቀም

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በኢንዶኔዥያ 50 ተጓዦችን አሳፍሮ ሲበር የነበረው ንብረትነቱ የስሪዊጃያ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 737 አውሮፕላን የደረሰበት አልታወቀም፡፡

አውሮፕላኑ ከኢንዶኔዥያ ዋና ከተማ ጃካርታ ከተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ነው መሰወሩ የተነገረው፡፡

መዳረሻውንም በሀገሪቱ ምዕራብ ካሊማንታን አውራጃ ወደ ፖንቲያክ ሲጓዝ እንደነበር ነው ባለስልጣናቱ የገለጹት፡፡

የሀገሪቱ የትራንስፖርት ሚኒስትር የነፍስ አድን ጥረት እና አሰሳ እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል፡፡

ስሪዊጃያ አየር መንገድ የሀገር ውስጥ በረራዎችን የሚያደርግ ሲሆን በጉዳዩ ዙሪያ መረጃዎችን በመስብሰብ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

ይህ አሁን የደረሰበት ያልታወቀው አውሮፕላን ከዚህ ቀደም ሁለት ከባድ አደጋዎችን ካስተናገደው ከ737 ማክስ ጋር ይለያያሉ ተብሏል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.