Fana: At a Speed of Life!

በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና በኢነርጂ ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የመሰማራት ፍላጎታቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቴክሳቫና ኩባንያ እና ኢኖቫተርስ ኢነርጂ የተባሉ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና በኢነርጂ ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች በዘርፉ በኢትዮጵያ የመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ።
ኩባንያዎቹ ይህንን የገለጹት በኬንያ ከሚገኘውየኢትዮጵያ ኤምባሲ ምክትል ሃላፊ ከአምባሳደር ሲራጅ ረሺድ ጋር ባደረጉት ውይይት ነው።
በዚህ ወቅት ኩባንያዎቹ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት መዋዕለ ንዋያቸውን የማፍሰስ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።
በወቅቱም አምባሳደር ሲራጅ ረሺድ ÷ ኢትዮጵያ ውስጥ ስላሉ ሰፊ የኢንቨስትመንት እድሎችና ማበረታቻዎች ገለጻ አድርገውላቸዋል።
ከዚህ ባለፈም ኤምባሲው ለኩባንያዎቹ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ መግለጻቸውን በኬንያ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.