Fana: At a Speed of Life!

በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ላይ ስርቆት በፈፀሙና ጉዳት ባደረሱ ግለሰቦች ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ላይ ስርቆት በፈፀሙና ጉዳት ባደረሱ 20 ግለሰቦች ላይ የቅጣት ውሳኔ መተላለፉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡
በአገልግሎቱ የሕግ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ አበበ ተስፋ÷ 20 ተከሳሾች ጥፋተኝነታቸው ተረጋግጦ ከ6 ወር እስከ 12 ዓመት በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑንና ቀሪዎቹ ክሶች በሂደት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው ግለሰቦች በተለያየ ወንጀል የተሳተፉ መሆናቸውን ገልጸው÷ የኤሌክትሪክ ገመድ የሰረቁ፣ በሕገ ወጥ መንገድ ቆጣሪ ያስገቡ፣ በምሰሶና በኤሌክትሪክ መስመር ላይ ጉዳት ያደረሱ ይገኙበታል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተፈፀሙ እና ከባለፈው በጀት ዓመት የተዛወሩ ተቋሙን ከ84 ሚሊየን ብር በላይ ያሳጡ 357 የተለያዩ የወንጀል ክሶች መመስረቱን የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.