Fana: At a Speed of Life!

በኤርትራ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር ተዘግተው የነበሩ ትምህርት ቤቶች ተከፈቱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኤርትራ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር ዝግታቸው የነበሩ ትምህርት ቤቶች መክፈቷን የሀገሪቱ ኢንፎርሜሽን ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረ-መስቀል አስታወቁ።

በመላ ሀገሪቱ ትምህርት ቤቶቹ የተከፈቱት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚያስችሉ ስርዓቶች በመዘርጋት መሆኑን ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የመማር ማስተማር ሂደቱ በክፍል ውስጥ መጨናነቅን መቀነስ በሚያስችል መልኩ በሶስት ፈረቃዎች እንደሚሰጡም ተገልጿል።

አካባቢያዊ  የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት ቁጥጥር ተግባራዊ እንደሚደረግም ነው ሚኒስትሩ ያስታወቁት።

ኤርትራ ከኮሮና ቫይረስ መከሰት በኋላ አገልግሎት አቁመው የነበሩ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችን ባለፈው ሳምንት ወደ ስራ ማስገባቷ የሚታወስ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.