Fana: At a Speed of Life!

በኤርትራ 4 ነጥብ 4 ሬክተር ስኬል የተለካ ርዕደ መሬት ተከሰተ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኤርትራ ሰሜን ምዕራብ አቆርዳት አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ ተገለፀ፡፡
የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገጻቸው እንዳሰፈሩት በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 4 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ መመዝገቡን ገልፀዋል፡፡
የማዕድን፣ ኢነርጂ እና የጂኦግራፊካል ላቦራቶሪን ጠቅሰው ባሰፈሩት ፅሁፍ የተጎዳ ሰውና የወደመ ንብረት የለም ብለዋል፡፡
የመሬት መንቀጥቀጡ ከሰሜን ምዕራብ አቆርዳት 91 ኪሎ ሜትር ላይ መፈጠሩንም አስታውቀዋል፡፡
የባለሙያዎች ቡድን ወደ ስፍራው እንደሚላክም ነው የገለጹት፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፦

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.