Fana: At a Speed of Life!

በኤጀርሳ ለፎ ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የስምንት ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ሸዋ ዞን ኤጀርሳ ለፎ ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።
የኤጀርሳ ለፎ ወረዳ ትራፊክ ፖሊስ ተቆጣጣሪ ዋና ሳጂን ፍቃዱ ሙሉጌታ ለኢዜአ እንደገለጹት አደጋው የደረሰው ትላንት ማምሻውን በወረዳው ለገ ሁሉቆ በተባለ አካባቢ ነው።
ከአዲስ አበባ ወደ ጊንጪ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ከአምቦ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ ከነበረ የህዝብ ማመላለሻ ቅጥቅጥ አይሱዙ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ አደጋው መድረሱን ተናግረዋል።
በአደጋው የሚኒባሱ አሽከርካሪን ጨምሮ ሚኒባሱ ውስጥ የነበሩ የ8 ሰዎች ህይወት ወዲያው ማለፉንም ተናግረዋል።
በሚኒባሱ እና በአይሱዙ ተሸከርካሪ ውስጥ የነበሩት ጉዳት የደረሰባቸው ስድስት ሰዎች በጳውሎስ ሆሲፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
በአደጋው ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች አስከሬን ለየቤተሰቦቻቸው መሰጠቱን የገለጹት ዋና ሳጂን ፍቃዱ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም አስታውቀዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.