Fana: At a Speed of Life!

በእሁድ ገበያ ከ25 ሚሊየን ብር በላይ የአምራች ሸማች የቀጥታ ግብይት ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሦስት ሣምንታት የእሑድ ገበያ የአምራች ሸማች የቀጥታ ግብይት ሰንሰለት በሸማች ኅብረት ሥራ ማኅበራት በኩል ከ25 ሚሊየን ብር በላይ ግብይት መፈፀሙን የአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ገለጸ።
በመዲናዋ እየጨመረ የመጣውን የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች ዋጋ ውድነት ለማቃለል የሸማች ኅብረት ስራ ማኅበራት ከመደበኛ ተግባራቸው ጎን ለጎን በየሣምንቱ እሑድ በተመረጡ ቦታዎች እያገበያዩ ይገኛሉ።
የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ የማቅረቡ ዓላማ ኅብረተሰቡን ከሰው ሰራሽ የገበያ አሻጥሮችና ያልተገባ የዋጋ ንረት መከላከል መሆኑ ተገልጿል።
ለእሑድ ገበያው ከተመረጡት መካከል ሜክሲኮ አደባባይ፤ ፒያሳ ማዘጋጃ ቤት ፊት ለፊት፣ ጀሞ ኮንዶሚኒየም፣ ቦሌ መገናኛ አደባባይ እና አቃቂ ቃሊቲ መናኸሪያ ፊት ለፊት ይገኙበታል።
በዚህም የሸማች ኅብረት ስራ ማኅበራቱ ከክልል አምራች ኅብረት ስራ ማኅበራት የግብርና ምርቶችን፤ ከፋብሪካዎች የኢንዱስትሪ ምርቶችን ለከተማዋ ነዋሪ በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ ችለዋል።
ማኅበራቱ በየሣምንቱ እሑድ ከጠዋቱ 1 ሠዓት ተኩል ጀምሮ ሙሉቀን በተገለጹት የግብይት ቦታዎች ኅብረተሰቡን በማገበያየት የኢኮኖሚ ጫናውን በማቃለል አስተዋጽኦ እያደረጉ እንደሆነም ተናግረዋል።
በቀጣይም የማኅበራቱን አቅም በማጠናከር የግብይት መዳረሻዎችን ቁጥር፣ የምርት አይነቶችና የአቅርቦት መጠን ለማሳደግ እየተሰራ ነው ማለታቸዉን ኢዜአ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.