Fana: At a Speed of Life!

በእስራኤል በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ማስተዋወቂያ የመርሀ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በእስራኤል ቴሌአቪቭ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የኢትዮጵያን ባህላዊ ምግብ ዲፕሎማሲ፣ እና የኢንቨስትመንት እና ቱሪዝም ማስተዋወቂያ መርሀ ግብር ተካሂዷል።

ቴል አቪቭ ያፎ በሚገኘው የፔሬዝ የሰላም እና ኢኖቬሽን ማዕከል  በተካሄደውበዚህ የምግብ ዲፕሎማሲ መርሀግብር ላይ÷ በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር ረታ ዓለሙ የኢትዮጵያን ምግብ ቤቶች አገራችን በማስተዋወቅ ያላቸውን ድርሻ በሚመለከት ገለጻ ሠጥተዋል።

በእስራኤል በሚገኙ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግብ ቤቶች ለእንግዶቹ የአትዮጰያ ምግብ ያቀረቡ ሲሆን የኪነጥበብ ባለሙያዎች ለታዳሚውን ባህላዊ ሙዚቃ አቅርበዋል።

የኢንቨስትመንት እና ቱሪዝም ማስተዋወቂያ መርሀ ግብሩ ዓላማ በኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት እና በእስራኤል የንግዱ ማህበረሠብ መሀል እውነተኛ እና ገንቢ ውይይት መፍጠር መሆኑን ተናግረዋል::

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ የተጀመሩት የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ማሻሻያዎች ሪፎርሞች፣ በኢትዮጵያ ያለው ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥርና የሠለጠነ የሰው ኃይል መልካም እድሎች መሆናቸውን ገልጸው÷ እስራኤላዊያን ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል::

በእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ክፍል ዳይሬክተር ሚስ ሚሃል ጉር አርዬህ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ሠፊ የሆነ የኢንቨስትመንት እድል ያለባት ሀገር መሆኗን ገልጸዋል።

እስራኤላዊያን ባለሀብቶች የእድሉ ተጠቃሚ  እንዲሆኑ መስሪያ ቤታቸው ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን አስረድተዋል::

እስራኤል በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለውን ሪፈርም እንደምታደንቅ እና ትብብር እንደምታደርግ ገልጸዋል::

በዚህ መርሃግብር የፓናል ውይይት በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሀብቶችና ባለሙያዎች ገለፃ አቅርበዋል።

መድረኩ የተዘጋጀው በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን፣ የቱሪስት መስህቦችን፣ የሀገራችን  አቅም በማስተዋወቅ ገጽታ መገንባት እንደዚሁም የቱሪስት እና ኢንቨስትመንት ፍሰትን ለመጨመር መሆኑን በማጠቃለያው ተገልጿል ::

በመርሀ ግብሩ ላይ በእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ክፍል ዳይሬክተር ሚስ ሚሃል ጉር አርዬህ ፣ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢንቨስትመንት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር ጀኔራል አምባሳደር አባቢን ጨምሮ  ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን እስራኤል ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.