Fana: At a Speed of Life!

በእስራኤል እና ፍልስጤም መካከል ያለው ግጭት ወደ ሙሉ ጦርነት እንዳያመራ ተሰግቷል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ከፈረንጆቹ 2014 በኋላ ከፍተኛውን ወታደራዊ እርምጃ እስራኤል እና ሀማስ አንዳቸው በአንዳቸው እየወሰዱ ይገኛሉ።

ፍልስጤማውያን የእስራኤል ወታደሮች በአል አቅሳ መስጊድ ገብተው ወስደውታል ያሉትን እርምጃ ተከትሎ የተጀመረው ግጭት የበርካቶች ህይወት እንዲልፍ እና የአካል ጉዳት እንዲደርስ አድርጓል ተብሏል።

እስራኤል በጋዛ በሚገኙ የሀማስ ወታደራዊ የማዘዣ ጣቢያዎች እና የጦር መሪዎች ላይ በፈፀመቻቸው የአየር ጥቃቶች ሰላማዊ ሰዎችን ጨምሮ የ53 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።

በተመሳሳይ ሀማስ ኢላማቸውን ወደ እስራኤል ግዛቶች ያደረጉ በርካታ ሮኬቶችን መተኮሱን አስታቋል።

በዚህም እስከ አሁን ስድስት እስራኤላውያን መገደላቸውን የዘገበው አልጀዚራ ከጋዛ ሰርጥ 1 ሺህ 500 ሮኬቶችን እንደተተኮሱ ተገልጿል።

በሌላ በኩል እስራኤል ከሀማስ የተተኮሱ 500 ሮኬቶችን እንዳከሸፈች ነው ያስታወቀችው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.