Fana: At a Speed of Life!

በእስራኤል የሚኖሩ ቤተ እስራኤላውያን፣ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መንግስት የወሰደውን ሕግ የማስከበር እርምጃ በመደገፍ በቴልአቪቭ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በእስራኤል የሚኖሩ የቤተ እስራኤል ማኅበረሰብ አባላት፣ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መንግስት በሕወሓት ጁንታ ላይ የወሰደውን ሕግ የማስከበር እርምጃ እና የመከላከያ ሠራዊት ያደረገውን ተጋድሎ በመደገፍ በቴልአቪቭ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄደዋል።

የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ከቴል አቪቭ፣ ከኢየሩሳሌም፣ ከቤርሼባ እና ከሌሎችም የእስራኤል ከተሞች የመጡ ሲሆን፣ ይህን ያስተባበሩት ከተለያዩ የማህበረሰቡ አደረጃጀቶች ውስጥ የተውጣጡ መሆኑ ታውቋል።

ሰልፉን ያዘጋጁት ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለፉት ሁለት ሳምንታት ጁንታውን በመደገፍ እና በመንግስት የተወሰደውን የሕግ ማስከበር እርምጃ በመቃወም ሰልፍ ያደረጉ ሰዎች ጥያቄ እንዳስቆጣቸው ገልጸዋል።

ሰላማዊ ሰልፈኞቹ በኤምባሲው ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት ተገኝተው ባቀረቡት ጥያቄ በእስራኤል የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር እና ልዩ መልእክተኛ አምባሳደር ረታ ዓለሙ ወደ ሕዝቡ በመሄድ ባስተላለፉት መልዕክት “መንግስታችን የወሰደውን ሕግ የማስከበር እርምጃ እና ለመከላከያ ሠራዊታችንን ያላቸሁን አክብሮት ለመግለጽ ድጋፍ ስላደረጋችሁ በመንግስት ስም አመሰግናለሁ” ብለዋል።

አያይዘውም ሕግ የማስከበር ዘመቻው በድል መጠናቀቁ ትልቅ ስኬት መሆኑን ጠቅሰው፣ በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት መሰረት በሕግ የሚፈለጉትን የጁንታው ቡድን አባላት ለሕግ ለማቅረብ መንግስት የሚያከናውነው ወንጀለኞችን የማደንና የመልሶ ግንባታ ምዕራፍ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በቀጣይ የመንግስት ዋና ትኩረት የትግራይ ሕዝብ አሁን ካለበት ሁኔታ እንዲወጣ የመልሶ ግንባታ ማከናወን፣ ከመኖሪያችው የተፈናቀሉ የተሰደዱ ዜጎችን ወደነበሩበት ቀዬ መመለስ መሆኑን ገልጸው እነዚህን ተግባራት በመደገፍ ከመንግስት ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።

የድጋፉ ተሳታፊዎች በመግለጫቸው በሰሜን እዝ ላይ በተፈጸመው ከባድ ክህደት እና ጥቃት ልባችን አዝኗል፤ የጁንታውን ቡድን ለፍትህ ከማቅረብ በተጨማሪ ቡድኑ በሕግ ሊታገድ ይገባል ሲሉ መጠየቃቸውን በእስራዔል የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያወጣው መረጃ ያመለክታል፡፡

በመጨረሻም ሰልፈኞቹ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት በወቅቱ ያሰባሰቡትን 17 ሺህ 200 የአሜሪካ ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ለኤምባሲው አስረክበዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.