Fana: At a Speed of Life!

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኖርዊች ሲቲ የመጀመሪያው ወራጅ ቡድን ሆኗል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ35ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜና እሁድ ተደርገዋል።

ቅዳሜ በተደረጉ ጨዋታዎች በዌስትሃም ዩናይትድ የተሸነፈው ኖርዊች ሲቲ ወደ ሻምፒየን ሺፑ መውረዱን ያረጋገጠ የመጀመሪያው ቡድን ሆኗል።

ጨዋታውን የመውረድ ስጋት ያለበት ዌስትሃም ዩናይትድ 4 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

በሌሎች ጨዋታዎች ሊቨርፑል ከበርንሌይ አንድ አቻ ሲለያይ ቼልሲ ደግሞ በሼፊልድ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

ቅዳሜ ምሽት ላይ ከብራይተን የተጫወተው ማንቼስተር ሲቲ 5 ለ 0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ራሄም ስተርሊንግ ሶስት ጎል በማስቆጠር ሃትሪክ ሰርቷል።

በማግስቱ እሁድ በተደረጉ ጨዋታዎች ደግሞ ቀትር ላይ ወልቭስ ኤቨርተንን አስተናግዶ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፎታል።

ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው አስቶንቪላ ደግሞ ክሪስታል ፓላስን አስተናግዶ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ማምሻውን የተደረገው ቶተንሃም ሆትስፐርስ እና የአርሰናል ጨዋታ የሰሜን ለንደን ደርቢ ጨዋታ በቶተንሃም 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ምሽት 3 ሰአት ላይ በተደረገ ጨዋታ ደግሞ በርንማውዝ ሌሲስተር ሲቲን 4 ለ 1 በማሸነፍ በፕሪሚየር ሊጉ ለመቆየት ቀጣይ ጨዋታዎችን ይጠባበቃል።

አስተንቪላ በ30፣ በርንማውዝ በ31፣ ዋትፎርድ እና ዌስትሃም በእኩል 34 እንዲሁም ብራይተን 36 ነጥቦችን በመያዝ በፕሪሚየር ሊጉ ለመቆየት ቀጣይ ሶስት ጨዋታዎችን ይጠባበቃሉ።

ቼልሲ በ60፣ ሌሲስተር ሲቲ በ59 እንዲሁም ማንቼስተር ዩናይትድ በ58 ነጥቦች ከ3 እስከ 5ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ በቀጣይ አመት የቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎን ለማረጋገጥ ተፋላሚዎች ናቸው።

ዛሬ ምሽት ማንቼስተር ዩናይትድ ሳውዝሃምፕተንን የሚያስተናግድ ሲሆን ጨዋታውን ማሸነፍ ከቻለ 3ኛ ደረጃን መረከብ ይችላል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.